ከወለድ ነፃ አገልግሎት
መደበኛ ዋዲዓ ያድ ሃማን
አባላት መደበኛ ዋዲያ ሃማን መደበኛ ቁጠባን እንደየአቅማቸዉ ከ 1000 ብር ጀምሮ ይቆጥባሉ፣ የኅብረት ሥራ ማህበሩ አባሉ ላስቀመተው መደበኛ ዋዲዓ ያድ ሃማን ቁጠባ ገንዘብ ወለድ አይከፍልም፣ አባሉ ከኅብረት ሥራ ማህበሩ ሲሰናበት በመደበኛ ዋድያ ያድ ሃማን የቆጠበው ገንዘብተመላሽ ይሆናል፣
ወለድ አልባ የፍላጎት ቁጠባ አይነቶች
የፍላጎት ቁጠባ አገልግሎቶች በአባሉ ሙሉ ፍላጎትና ጥያቄ የሚሰጡ አገልግሎቶች ሲሆን አባሉ ገንዘቡን በሚፈልግበት ወቅት ከኅብረት ሥራ ማህበሩ በሚኖረው ስምምነት መሰረት ወጪ ሆነው የሚከፈሉ ናቸው፣
ቀርድ ቁጠባ
የፍላጎት ቀርድ ቁጠባ አንዱ የወለድ አልባ የቁጠባ አገልግሎት ሲሆን አባሉ ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ በፍላጎቱ የሚቆጥበው የቁጠባ ዓይነት ነው፣ ቀርድ ቁጠባ ሂሳብ አባላት በራሳቸው ፍላጎት ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይና ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ የማይጠየቅበት ወይም ትርፍ የማያስገኝ የቁጠባ ሂሳብ ሲሆን በውሉ መሰረት አባላት ገንዘቡን በከፊል ሆነ በሙሉ ማግኝት የሚችሉበት አሰራር ነው፣
የፍላጎት ዋዲዓ ያድ ሃማን
በአባሉ እና በኅብረት ስራ ማህበሩ ስምምነትና የሸሪዓ ህግ በሚፈቅደው መሰረት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበሩ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ አማራጮች ላይ ገንዘቡን እንዲያውል በመፍቀድ የሚከፈት የአደራ ቁጠባ ሂሳብ ነው፣ አባሉ ገንዘቡን በሚፈልግበት ወቅት የማግኘት መብት አለው፡፡ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበሩ በዚህ ቁጠባ አይነት ለተቀመጠ ገንዘብ ዋስትና ይሰጣል፣ አባሉን ለማበረታታት ሲባል ኅብረት ሥራ ማህበሩ የተለያዩ የዓይነት ሽልማቶችን መስጠት ይችላል፣
ዋዲዓ የልጆች ቁጠባ
ዋዲዓ የልጆች ቁጠባ አንዱ ወለድ አልባ ቁጠባ አካል ሲሆን ይህ የቁጠባ አይነት የአባላት ልጆች የቁጠባ ባህል እንዲያዳብሩ ለማድረግና ሃይማኖታዊ ቱውፊት የሆነውን የወለድ አልባ የቁጠባ አሰራር እውቀት ኖሯቸው እንዲያድጉ ለማስቻል ነው፣ ይህ አይነት የቁጠባ አሰራር ወለድ የማይታሰብበት ሆኖ ኅብረት ሥራ ማህበሩ ለአባላት ትርፍ በሚያስገኙ የስራ ዘርፎች በሸሪዓው መሰረት ሊያውለው ይችላል፣ ኅብረት ስራ ማህበሩ ከሚገኘው ገቢ ላይ ልጆችን ለማበረታት ሲባል የተለያዩ ሽልማቶችን አዘጋጅቶ መስጠት ይችላል፡፡
ዋዲዓ የህክምና ቁጠባ
የህክምና ቁጠባ የወለድ አልባ ቁጠባ ሲሆን አባሉ የጤና እክል በሚገጥመው ወቅት ለመታከሚያ ታስቦ የሚቀመጥ የቁጠባ አይነት ነው፣